ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር መስጠት የየዕለት ተግባር ሊሆን ይገባል።
ሰንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር የሉዓላዊነት መገለጫ ነው። በመለዮ ለባሹ ዘንድ ደግሞ የህይወት መስዋዕት ጭምር ስለሚከፍልለት ለሰንደቅ አላማ ልዩ ክብር ይሰጣል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሰንደቅ አላማ የሚገባውን ክብር ሰጥቶ የማውጣት እና የማውረድ ስነ-ስርዓት ማከናወን እየተቀዛቀዘ ቆይቷል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያካሄደ ያለውን ሪፎርም ተከትሎ ለሰንደቅ አላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ከፖሊስ ዋና መስሪያ ቤቱ ጀምሮ እስከ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ድረስ ጠዋት እና ምሽት ሰንደቅ ዓላማ የማውጣትና የማውረድ ስነ-ስርዓት ያለማቋረጥ መከናወን እንደሚገባ ተደርጓል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤትም በክብር ዘብ በማጀብ እንዲሁም ግራ እና ቀኝ ሰንደቅ ዓላማውን የሚያጅቡና ሰንደቅ አላማ የሚያወጡ እና የሚያወርዱ የፖሊስ አባላት ሰንደቅ ዓላማዎቹን በክብር ይዘው በቦታው ይገኛሉ።
ፊሽካ ይነፋል፤ እግረኛም ሆነ ተሽከርካሪ ባለበት ይቆማል፤ ሁሉም በያሉበት ለሰንደቅ ዓላማው ክብር ሰጥተው ስነ-ስርዓቱን ይከውናሉ።
ይህ የሰንደቅ አላማ የማውጣት እና የማውረድ ስነ-ስርዓት የአማራ ክልል ፖሊስ ከሚከውናቸው የየዕለት ተግባራት አንዱ ሆኖ ቀጥሏል።












