ለአማራ ክልል ፖሊስ ስትራቴጅክ እና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ለአማራ ክልል ፖሊስ ስትራቴጅክ እና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

የአማራ ክልል ፖሊስ ስትራቴጅክ እና ከፍተኛ አመራሮች የፖሊስ አመራር እና የፖሊስ ተቋም ሪፎርም ላይ ያተኮረ ስልጠና በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ፖሊስ ወቅቱን የሚመጥንና የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ መምራት የሚችል መሆን አለበት ብለዋል።

እንደ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገ /ሚካኤል ገለጻ ፖሊስ ከዘረኝነት የፀዳ፣ ትዕዛዝ የሚቀበል፣ በአመለካከቱ የተስተካከለ አና በጥሩ ስነ ምግባር የታነጸ መሆን አለበት።

መለዮ የለበሰ ሰው ሀገሩን መውደድ እና የሀገሩን ክብር መጠበቅ አለበት የሚሉት ኮሚሽነር ጀኔራሉ ፖሊስ ለህዝብ እና ለህሊናው ታምኖ ማገልገል ይጠበቅበታል ሲሉ በመክፈቻ ንግግራቸው አሳስበዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው የፖሊስ አመራር ተከታዮችን የሚያፈራ ለሌሎች አርአያ መሆን የሚችል መሆን አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

‘በጀግንነት መጠበቅ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!’ የፖሊስ ዋነኛ እሴት መሆኑን ያስታወሱት ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መስፍን አበበ ይሄን ተገንዝቦ ለህዝብ ሰላም እና ደኅንነት መረጋገጥ እስከ ህይወት መስዕዋትነት የሚከፍል የፖሊስ ሰራዊት መሆን ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ‘Conceptual of security’ በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጥተዋል።

ስልጠናው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለአንድ ሳምንት ሲሰጥ የሚቆይ ይሆናል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top