የመንግስትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂ ቡድኖች እጅ መስጠታቸው ተገለጸ

የመንግስትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂ ቡድኖች እጅ መስጠታቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንጎለላ ጠራ፣ በባሶና ወራና እና አሳግርት ወረዳዎች ጫካ ገብተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የህገ-ወጥ በድን አባላት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በሰላም እጅ መስጠታቸው ተገልጿል።

በሦስቱም ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የአንድ አማራ ፋኖ በሸዋ የነጎርጓድ ክፍለ ጦር በሚል አለሙ ሀብቱ የተባለ የቡድኑ ሀላፊና አዛዠ በመሆን ሲመራ የነበረውን 13 የቡድኑ አባላትን ጨምሮ አንጎለላና ጣራ ወረዳ አሳባህር ቀበሌ ለጥምር ጦሩ እጃቸውን ሰጥተዋል።

የቡድኑን አባላት ድሽቃ መሳሪያ 1 ከመሰል 295 ጥይት ከ5 ሸንሸል፣ ብሬን መሳሪያ 4 ከመሰል 839 ጥይት 6 ሸነሸል፣ ስናይፐር 1 ከ6 ካዝና 44 ጥይት፣ ክላሽ መሳሪያና 6 ከካርታ 22 እና 549 ጥይት፣ ኤስ ኬይ ኤስ እና ቃታ መሣሪያ 6፣ የአጅ ቦንብ 8 እና የተለያዩ ካዝና 22 ሸንሸል 4 በአጠቃላይ 17 የተለያዩ የጦር የመሣሪያ እና ሌሎች ተተኳሽ ጥይቶችን በመያዝ በፍቃደኝነት እጅ ሰጥተዋል።

ትግሉ አዋጭነት ስለሌለው ሌላውም ከኛ ይማር። እኛም ከእንግዲህ የበደልነውን ህዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን ሲሉ በሰላም እጅ የሰጡት የታጣቂ በድን አባላት ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top