ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

ለሽብር ወንጀል ሊውል የነበረ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ዋለልኝ ቢምረው እንደገለጹት መነሻውን ምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ኢት 83527 የሆነ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ለሽብር ወንጀሎች መፈጸሚያ ሊውሉ የነበሩ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እንደ ኮማንደር ዋለልኝ ገለጻ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር በብሔራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም በጸጥታ ግብረ ኃይሉ ክትትል 02 ስናይፐር፣ 01ብሬን፣ 02 የከርከር መሳሪያ፣ 6 ሺህ 658 የብሬን ጥይት፣ 7ሺህ 889 የክላሽ ጥይት፣ 256 የከርከር መሣሪያ ጥይት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ከህገ-ወጥ የጦር መሳሪያው ጋር ሶስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው የባህርዳር ከተማ አስተዳድር ፖሊስ መምሪያ ተጨማሪ ምርመራ በማካሄድ ላይ መሆኑን ኮማንደር ዋለልኝ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ከህገ-ወጥ ድርጊት እራሱን እንዲያርቅ እና መሰል የወንጀል ድርጊት ሲመለከትም ለህግ አካል ሊያሳውቅ ይገባል ሲሉ ኮማንደር ዋለልኝ ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ሚዲያን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ለመከታተል ከስር ያሉ ሊንኮችን ይጠቀሙ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top