የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄደ።

ፖሊስ መምሪያው በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ስራዎችን የወረዳ እና የዞን አመራሮች በተገኙበት ገምግሟል።

የዞኑን ሠላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ ስራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የፖሊስ ሰራዊቱ በሁሉም ወረዳ በጥምር ጦር ተደራጅቶ በመሰማራት በጠላት ላይ የበላይነት በመዉሰድ ሰላምና ጸጥታን ማስፈን መቻሉ፤

አጋዥ የጸጥታ ኃይሎችን አሰልጥኖ በማሰማራት ለጸጥታ ስራው መጎልበት የድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረጉ፤

ከ430 በላይ የወንጀል መዝገቦችን መርምሮ በማጣራት ለሚመለከተው የፍትህ አካላት መላኩ እንዲሁም ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎችን በማስተማር በትምህርት ሊታለፉ የማይችሉትን ደግሞ እርምጃ መውሰድ መቻሉ በግምገማው ላይ በጥንካሬ ተመላክቷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያካሄደ ያለውን የሪፎርም ስራ ተቀብሎ እስከ ወረዳ ድረስ ተግባራዊ በማድረግ ለአማራ ህዝብ ሰላም እና ደኅንነት መረጋገጥ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተሳታፊዎች በመድረኩ አጽንዎት ሰጥተው መናገራቸውን ከማዕከላዊ ዞን ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top