የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰላም እጅ መስጠታቸው ተገለጸ

የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በሰላም እጅ መስጠታቸው ተገለጸ

‎በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ በወረሞ ዋጅቱ ንዑስ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 55 ህገወጥ ታጣቂ ቡድኖች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል በአካባቢው ለሚገኘው ጥምር ጦር በሰላማዊ መንገድ እጅ መስጠታቸው ተገልጿል።

ታጣቂዎቹ እስከ ዛሬ ድረስ በተሳሳተ መንገድ ወደ ህገወጥ ቡድኑን ተቀላቅለው ቢቆዩም የወጡበት ዓላማ ትክክል አለመሆኑን በመረዳት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ለመንግስት እጃቸውን ሰጥተዋል።

ህገወጥ ቡድኖች እንደተናገሩት ትግሉ አላማ የለሽ እና የአማራን ህዝብ ለከፋ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ችግር የሚዳርግ መሆኑን በመረዳት በሰላም እጃችንን ሰጥተናል። በቀጣይም ከጥፋታችን ተምረን የበደልነውን ህዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን ብለዋል።

መረጃው የሚዳ ወረሞ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው።

የአማራ ክልል ፖሊስ ሚዲያን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ለመከታተል ከስር ያሉ ሊንኮችን ይጠቀሙ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top