የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ደረጃ ማደጉ ተገለጸ።
የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅን ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ደረጃ ማደጉን አስታውቋል።
ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ ታህሳስ ወር 1985 ዓ.ም የአማራ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም በሚል ተመስርቶ ለ14 አመታት ማሰልጠኛ ተቋም ሆኖ ቆይቷል።
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2017 ሰኔ 5 ድርስ ደግሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ሆኖ ቆይቷል።
የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅን ከሰኔ 05/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ደረጃ በማግኘቱ አሁን ላይ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ ሆኗል።
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ እስካሁን በምልምልነት፣ በሰርተፊኬት እና በዲፕሎማ መርሐ ግብር ብቁ የፖሊስ አባላትን እና መኮንኖችን ሲያስመርቅ መቆየቱም ነው የተገለጸው።
አሁንም ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በማደጉ ብቁና ከዘመኑ ጋር የሚራመድ ፖሊስ ለማፍራት እንዲሰራ ያስችለዋል ተብሏል።

