“የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ በህዝብ እና ፖሊስ መካከል የሚኖር ግንኙነትን ማጠናከር ይገባል” ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ

“የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ በህዝብ እና ፖሊስ መካከል የሚኖር ግንኙነትን ማጠናከር ይገባል” ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ

ከምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ እና ከደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አመራሮች ጋር በወቅታዊ እና በመደበኛ የፀጥታ ስራዎች አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ውይይት በደብረማርቆስ ከተማ ተካሂዷል።

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ እና የአድማ መከላከል ፖሊስ ምክትል ዋና መመሪያ ኃላፊ ኮማንደር ልጅ አዱኛ ሙልጌታ ተገኝተዋል።

ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ እንደገለጹት “የማህበረሰብን ተሳትፎ በማሳደግ በህዝብ እና ፖሊስ መካከል የሚኖር ግንኙነትን ማጠናከር ይገባል” ብለዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የለውጥ ስራዎችን በመገንዘብ ህዝቡ ለሚፈልገው ፍትህ እና ደህንነት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ሲሉ ረዳት ኮሚሽነር አበበ ተናግረዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው፤ ለሰላም መስፈን ደግሞ ፖሊስ ግንባር ቀደም በመሆን ለማህበረሰቡ በታማኝነት አገልግሎት መስጠት ይገባል ያሉት ደግሞ የአድማ መከላከል ፖሊስ ምክትል ዋና መመሪያ ኃላፊ ኮማንደር ልጅ አዱኛ ሙልጌታ ናቸው።

በውይይቱ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መመሪያ አመራሮች፣ የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አመራሮች እንዲሁም በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሁሉም ጣቢያዎች እና የጎዛምን ወረዳ ፖሊስ አመራሮች ተገኝተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top