“በጥብቅ ዲሲፕሊን በመመራት በእውቀት፣ በህዝብ አገልጋይነት ስሜት እና በክህሎት የበቃ ፖሊስ እንገነባለን” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

“በጥብቅ ዲሲፕሊን በመመራት በእውቀት፣ በህዝብ አገልጋይነት ስሜት እና በክህሎት የበቃ ፖሊስ እንገነባለን” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ከጎንደር ከተማ፣ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን እንዲሁም ከአድማ መከላከል ፖሊስ አመራሮች ጋር በጎንደር ከተማ ተገኝተው ውይይት አካሂደዋል።

ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በውይይቱ አንደገለጹት “በጥብቅ ዲሲፕሊን በመመራት በእውቀት፣ በህዝብ አገልጋይነት ስሜት እና በክህሎት የበቃ ፖሊስ እንገነባለን” ብለዋል።

እንደ ኮሚሽነር ዘላለም ገለጻ ህዝብን ሰላም ለመንሳት በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ የማያዳግም ዕርምጃ በመዉሰድ የተሰጣችሁን ተልዕኮ በድል መወጣት ይገባል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያካሄደ ያለው የሪፎርም ስራ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ይታይ የነበረውን መቀዛቀዝ በማስቀረት ተቋሙ ወደ ነበረበት ከፍታ ለመመለስ የሚያስችል ነው በማለት ኮሚሽነር ዘላለም በአጽንኦት አብራርተዋል።

በሪፎርሙ ለአመራሩም ሆነ ለአባሉ ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናን በመስጠት ዕውቀትን፣ አስተሳሰብንና ክህሎትን ማስተሳሰር፣ መቅረፅ እና ማስተካከል ላይ በትኩረት ይሰራል ሲሉ ኮሚሽነር ዘላለም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በሪፎርም ስራዎች፣ በስትራቴጂ፣ በመዋቅር እንዲሁም በአሰራር ረገድ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት ሲመዘኑ ስር-ነቀል ሪፎርም እየተካሄደ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ የክልሉ ፖሊስ ከነበረበት ችግር ወጥቶ የተሻለ የመፈፀም አቅም እንዲፈጥር የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስን በቴክኖሎጂ ብቁ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀምና ነባሮችን የማስፋት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በቀጣይም የአማራ ክልል ፖሊስን የሚያጠናክሩ ስራዎችን በተለይም የፖሊስ ሠራዊታችን ግዴታውን ብቻ ሳይሆን መብቱም በተገቢው መልኩ የሚከበርበት እንዲሁም እየተከናወኑ ባሉ የሪፎርም ስራዎች ውጤት የሚመዘገብባቸውን የፕሮፌሽናሊዝም ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ለተወያዮቹ ተናግረዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top