በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተካሄደው ህዝባዊ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል።

ህዝባዊ ሰልፉ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።

በአማራ ክልል በሚገኙ በሁሉም ዞኖች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ወረዳዎች የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል።

ፕሮግራሙ በሰላም እንዲጠናቀቅ ደግሞ የሰላማዊ ሰልፉ ታዳሚዎች ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም እና ተገቢውን ትብብር በማድረጋቸው ነው።

ህብረተሰቡም የፀጥታው ጉዳይ ይመለከተኛል የሚል አስተሳሰብ በመያዝ ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ እና ለፀጥታ ስራው ስኬታማነት ጉልህ የድርሻውን ተወጥቷል።

ስለሆነም ለመላው የክልሉ ህዝብ እንዲሁም የዛሬውን ሰልፍ ላስተባበሩ እና ለመሩ አካላት በሙሉ ፖሊስ ምስጋና ያቀርባል።

አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ሳይበግራችሁ ለህዝብ ሰላም እና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ኃላፊነታችሁን በአግባቡ እየተወጣችሁ ለምትገኙ የፌደራል የፀጥታና የደህንነት ተቋማት ፣ከክልሉ የፀጥታ አካላት በጋራ በቅንጅት ሂደቱን የመሩበት መንገድ በሙሉ የአማራ ክልል አካባቢዎች በተሳካ ሁኔታ በመፈፀሙ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የላቀ ምስጋናውን ያቀርባል።

በመጨረሻም የአማራ ህዝብ ለሰላም እና ደህንነት ያለውን ቀናኢነት በማጎልበት፤ እንደሁልጊዜው ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም የክልሉን ሰላም በዘላቂነት ማስጠበቅ እንደሚገባ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጥሪ ያቀርባል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top