በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ በጥምር ጦሩ በተደረገ ኦፕሬሽን ከህገ-ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያ ተማረከ።

በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ በጥምር ጦሩ በተደረገ ኦፕሬሽን ከህገ-ወጥ ቡድኖች የጦር መሳሪያ ተማረከ።

በእስቴ ወረዳ ህገ-ወጥ ቡድኖች በሚንቀሳቀሱባቸው ቀበሌዎች ጥምር ጦሩ ባካሄደው ልዩ ኦፕሬሽን 18 ክላሽኮቭ፣ 5 የቃታ እና 3 ፋል የጦር መሳሪያዎች መማረኩን የእስቴ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የጸጥታ ኃይሉ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን በሚያደርገው ህግ የማስከበር እና ፍትህን የማረጋገጥ ስራ ላይ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት የጥምር ጦሩ መሪዎች በቀጣይም በህገ-ወጥ ቡድኑ ላይ በሚወሰደው የተጠናከረ እርምጃ ህዝቡ የተለመደ ድጋፉን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top