የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኪነት ቡድን ተደራሽነታቸውን በማስፋት የተሻለ ኪነ-ጥበባዊ ስራዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኪነት ቡድን ተደራሽነታቸውን በማስፋት የተሻለ ኪነ-ጥበባዊ ስራዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኪነት ቡድን በተውኔት እና በሙዚቃው ዘርፍ አንቱ የተሰኙ ተዋንያን እና ከያኒያንን ያፈራ ይገኛል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኪነት ቡድን ሰራዊቱ በሚገኝበት ቦታዎች ሁሉ በመገኘት በሞራል እና በስነልቦና የጠነከረ ኀይል እንዲሆን በማነቃቃት እና ሞራል በማስታጠቅ እንዲሁም ጀብደኝነትን በማበረታታት ተግባሩን እየተወጣ የሚገኝ የፖሊስ ኪነት ቡድን ነው።

የኪነት ቡድኑ ለሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን ከሀገር ወጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ህዝቡን እያዝናኑ የሚያስተምሩ ጥበባዊ እና ኪናዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የሰላም፣ የልማት እና የእድገት አጋርነቱን አሳይቷል፤ የክልሉን ብሎም የኢትዮጵያን ባህል እያስተዋወቀ ይገኛል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያካሄደ ባለው ሪፎርም የኪነት ቡድኑ ተደራሽነታቸውን ለማስፋት እና የተሻለ ኪነ-ጥበባዊ ስራዎችን ለሰራዊቱ እና ለህዝብ ማራኪና ሳቢ በሆነ መንገድ እንዲያቀርብ በሚያስችል ሁኔታ ተደራጅቶ ይገኛል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top