በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደብረማርቆ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ገለጸ።
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በተድላጓሉ ክፍለከተማ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታው የቦቅላ መገንጠያ እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ መነሻውን ከደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ያደረገ በጭነት አይሱዙ 3011(ስስት ሽህ አስራ አንድ) ሊትር ህገወጥ ነዳጅ በአካባቢው በስራ ስምሪት ላይ በነበሩ የፀጥታ ሀይሎች ከነ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውሏል።
ድርጊቱን በተፋጠነ በማጣራት ለሚመለከተው የፍትህ አካል ለመላክ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን በከተማ አስተዳደሩ የ2ኛ ፖሊስ ጣቢያ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ተወካይ ሀላፊ ዋና ሳጅን እስማኤል ገልጸዋል ።
ወቅታዊ ሁኔታውን እንደምቹ ሁኔታ በመጠቀም በህገወጥ መንገድ ሀብት ለማካበት በማሰብ በከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ህብረተሰቡ መንግስትን እንዲያማርር ደላላ እና ነዳጅ ማደያዎች በትስስር የተፈፀመ ወንጀል በመሆኑ በህግ አግባብ ተገቢውን ቅጣት ለማሰጠት እየተሰራ መሆኑን ዋና ሳጅን እስማኤል አስረድተዋል ።
ህብረተሰቡ በህገወጥ መንገድ ነዳጅ ሲቀዳ በሚመለከትበት ወቅት በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች ጥቆማ በመስጠት የሁልግዜ ትብብር እንዲያደርግም ተጠይቋል ።



