በላይ ጋይንት ወረዳ በተሰማራው ጥምር ጦር በህገ-ወጥ ቡድኑ የተዘረፈ 25 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ተያዘ።
በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ ሳሊ ቀጠና የተሰማራው ጥምር ጦር በአካሄደው ህግ የማስከበር ተግባር በህገወጥ ቡድኑ የተዘረፈ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ቁሳቁሶች ተይዘዋል።
ህገ-ወጥ ቡድኑ ከነፋስ መውጫ ከተማ ደብረታቦር ባለው ዋና መንገድ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎችን፣ አሽከርካሪዎችን እና ተጓዦችን እያገተ የዝርፊያ ወንጀል ሲፈፀም ቆይቷል።
የሀገር መካላከያ ሰራዊት ከወረዳው የፀጥታ መዋቅር እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት በቀጠናው እየወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ርምጃ 25 ሚሊየን ብር የሚገመት የውሃ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፓምፖች፣ ኬብሎች እና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ከህገ-ወጥ ቡድኑ መሪ አይናለም ጥላሁን ቤት ተይዛል።
በቀጠናው እየተሰራ ለሚገኘው ህግ የማስከበር ተግባር ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ መልካም እንደሆነ የገለጸው የላይ ጋይንት ወረዳ ኮሙኑኬሽን ጽሕፈት ቤት ጥምር ጦሩ በህገ-ወጥ ቡድኑ ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ሚዲያን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ለመከታተል ከስር ያሉ ሊንኮችን ይጠቀሙ።




