በጦር መሣሪያ በመታገዝ በእገታ ወንጀል የደብረ ማርቆስን ሕዝብ ሲያሰቃዩ የነበሩ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ ።

በጦር መሣሪያ በመታገዝ በእገታ ወንጀል የደብረ ማርቆስን ሕዝብ ሲያሰቃዩ የነበሩ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ ።

ነዋሪነታቸው በደብረ ማርቆስ ከተማ የሆኑት 1ኛ ላመስግን ካክች አስማረ 2ኛ እሱባለው ጥበብ አስማረ እና 3ኛ እድሜዓለም ታገለ ይርዳው የተባሉ ግለሰቦች መጋቢት 10/2017 ዓ.ም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በጦር መሳሪያ በመታገዝ በደብረ ማርቆስ ከተማ ከአንዲት ግለሰብ መኖሪያ ቤት ገብተው እና አግተው አንድ ሚሊዮን ብር እንድትሰጣቸው ተደጋሚ በማስፈራት ጫና እያሳደሩ በነበሩበት የደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባልደረቦች በደረሳቸው ጥቆማ ክትትል ይጀምራሉ።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ አባላት በፖሊሳዊ ጥበብ ክትትላቸውን በማጠናከር በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ተሾመ ብዙ ግለሰቧ ጥቆማ እንደጠች ጠንካራ ፖሊሳዊ ክትትል በማካሄድ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ግለሰቦች በከተማው የእገታ፣ የዘረፋ እና የግድያ ወንጀሎችን እንደሚፈጽሙ ተጠቁሞ ሲፈለጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ከግለሰቦቹ አንዱ የታጣቂው ቡድን አባል ኾኖ ሰላምን ሲያደፈርስ የቆየ እና ይቅርታ ጠይቆ የገባ እንደኾነም ገልጸዋል።

ግለሰቦቹ ገንዘብ ሊቀበሉ እጅ ከፈንጅ ከተያዙ በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው በተደረገ ፍተሻ ሁለት ክላሽ ከ55 ጥይት ጋር፣ አንድ ሽጉጥና ጎራዴ መገኘቱን ኮማንደሩ ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የተጠለሉበት ቤት የአንደኛው ግብረ አበራቸው እንደኾነ እና ሁሉም የተያዙ መሳሪያዎች ቤት ውስጥ ተቆፍሮ ተደብቀው እንደተገኙም ገልጸዋል።

ለተፈጸመው ወንጀል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የምርመራ ቡድን በማደራጀት እና አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ እና በማጠናከር መዝገቡን አጠናቆ ለምስራቅ ጎጃም ዞን አቃቢህግ መምሪያ በመላክ ክስ መመስረት መቻሉን አስረድተዋል ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 3/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾች ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተከብሮ ክርክር ሲያደርጉ ቆይተው የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ሊያስተባብሉ ባለመቻላቸው እና ወንጀሉን ስለመፈጸማቸው በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ 1ኛ እድሜዓለም ታገለ በ21 አመት እስራት እና በ2ሺ ብር 2ኛ ላመስግን ካክች አስማረ በ16 አመት እስራት እና በ2 ሺብር 3ኛ እሱባለው ጥበቡ አስማረ በ15 አመት እስራት እና በ2 ሺብር መቀጣታቸውን ገልጸዋል ።

ተከሳሾቹ በሌላ እገታ ወንጀል 6 መቶ ሺ ብር በመቀበል በፈጸሙት የውንብድና ወንጀል ምርመራ ተጣርቶባቸው በፍርድ ሂደት ላይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል ።

ለጸጥታ ሀይሉ መረጃ ከመስጠት ጀምሮ ፣ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለአዋሉ የጸጥታ ሀይሎች ፣ለመርማሪዎች እና ለሁሉም የፍትህ አካላት ህዝብ እና መንግስት የጣለባቸውን ሀላፊነት በአግባቡ በመወጣት ለአከናወኑት ተግባር ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ህብረተሰቡ ወንጀል ሲፈጸም ሲያዩ ለጸጥታ ሀይሉ መረጃ መስጠት የሚገባ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል ።

መረጃው፡-የደብረማርቆስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top