“ሪፎርም ሲባል የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በመቅረፍ የተሻለ የአሰራር ዘይቤ ማምጣት መቻል ነው” ረዳት ኮሚሽነር አበበ ደለለ የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር

“ሪፎርም ሲባል የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በመቅረፍ የተሻለ የአሰራር ዘይቤ ማምጣት መቻል ነው” ረዳት ኮሚሽነር አበበ ደለለ የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር

ሪፎርም ማለት አሉ ረዳት ኮሚሽነር አበበ ደለለ በፊት ከነበሩ የአሰራር ክፍተቶች በመውጣት የተፋጠነና የተሻሻለ የህዝብ አገልግሎት ለመስጠት ያስችል ዘንድ አዲስና ውጤት አምጭ የአሰራር ስልትን መከተል እንጂ የሰው ኃይል ቅነሳ ማለት አይደለም ብለዋል።

በአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እየተተገበረ የሚገኘው የሪፎርም ስራ እርሾ ከተጣለባቸው ክፍሎች ቀዳሚው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ መሆኑንም አንስተዋል።

ፖሊስ ኮሌጁ የሪፎርሙን ንድፈ ሀሳብ ከማዘጋጀት ጀምሮ ልዩ ልዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በመስራት ለዋና ጠቅላይ መምሪያ የጀርባ አጥንት ነው ብለዋል።

የፖሊስ የቀደመ ክብርና ከፍታ ይመለስ ዘንድ ሪፎርሙ ትልቅ ሚናን ያበረክታል ተብሎ ይታሰባል ስለሆነም ሁሉም የፖሊስ ሰራዊት በሪፎርሙ ልክ ራስን ማብቃትና ማዘጋጀት ያስፈልጋል ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

ከቀጣይ የፖሊስ ኮሌጁ የ100 ቀን ዕቅዶች ጋር ተያይዞም ላነሳንላቸው ጥያቄ ኮሌጁ የደረሰበትን ጉዳት በማስተካል ከወታደራዊ ስልጠናና ዲፕሎማ መርሃ ግብሮች በተጨማሪ በዲግሪ መርሃ ግብር ስልጠና ለመጀመር ጥናት ተደርጎ ከሚፈጸሙ ዕቅዶች የመጀመሪያው ነው ብለዋል።

የ34ኛ ዙር መደበኛና አድማ መከላከል ፖሊስ ስልጠናንም በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቅ ሌላው ዕቅዳችን ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በዋና ጠቅላይ መምሪያው መመሪያ መሰረት የማዕረግ ሽግግር ስልጠናም ለመስጠት ዕቅድ ይዘናል ነው ያሉት።

የቀጣይ የ100 ቀን ዕቅዳችን እንዲሳካና የሪፎርም ስራው ፍሬያማ ይሆን ዘንድ ከመቸውም በላይ ጥረት ያስፈልጋል፤ የሚመለከታቸው አካላትም ኮሌጁን መልሶ ማቋቋም ይቻል ዘንድ አስፈላጊ ድጋፍ ማድረግ ይኖባቸዋል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top