የበቃ የፖሊስ ሰራዊት እንዲኖር የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎችን ፍጥነት ወደ ግብ ማድረስ እንደሚገባ ተገለጸ

የበቃ የፖሊስ ሰራዊት እንዲኖር የተቋማዊ ሪፎርም ስራዎችን ፍጥነት ወደ ግብ ማድረስ እንደሚገባ ተገለጸ

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ ለክቡር የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የዋና ጠቅላይ መምሪያው ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የቢሮ እድሳትና ግንባታ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ አስጎብኝተዋል ።

ክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ እየተከናወኑ ያሉ የለውጥ ስራዎችን ለእንግዶች ተዘዋውረው ያስመለከቱ ሲሆን የተለወጠ የፖሊስ ተቋም እንዲኖር የተቋማዊ የሪፎርም ስራዎችን በተሻለ ፍጥነት ወደ ግብ ለማድረስ ሁሉን አቀፍ የፖሊስ የለውጥ ትግበራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለእንግዶች በገለፃቸዉ አንስተዋል።

የተቋም ግንባታ ስራዎቻችን የተሻለ የህዝብ አገልግሎትን ለማስፈን ወሳኝ መሆናቸውን የገለፁት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እየተከናወኑ ባሉ የለውጥ ስራዎች ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የፖሊስ ተቋም አለም አቀፋዊ ሆኖ የተቋቋመ መሆኑን ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ በብዙ ችግሮች አገልግሎት እየሰጠ ዛሬ ላይ ቢደርስም ዘመኑን የዋጀ የተሻለ የአገልግሎት እንዲሰጥ ምቹ የስራ ሁኔታ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የተጀመሩ የቢሮ እድሳትና ግንባታዎች በቴክኖሎጅ ታግዘው የተሻለ የፖሊሰ ተቋም መገንባት አሰፋላጊ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በአፅንኦት አንስተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top