ከ1 ሺህ 200 ሊትር በላይ ህገ-ወጥ ቤንዚን መያዙን ፖሊስ ገለፀ።
በባህርዳር ከተማ አስተዳደር በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ ለግብይት ሊውል የነበረ ቤንዚን መያዙን በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢንስፔክተር የሽዋስ ገበየሁ ተናግረዋል።
እንደ ኢንስፔክተር የሽዋስ ገበየሁ ገለጻ ከማህበረሰቡ በተገኘ ጥቆማ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከ6 የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ ሊሸጥ የነበረ ከ1ሺህ 200 ሊትር በላይ ቤንዚን ተይዟል ብለዋል።
ከወንጀል ድርጊቱ ጋር በተገናኘ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው የሚገኝ ሲሆን ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በክትትል ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ከህዝቡ የሚደበቅ ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት እንደሌለ የተናገሩት ኢንስፔክተር የሽዋስ ሁሉም ማህበረሰብ ህገ-ወጥ ተግባርን በመፀየፍ የሚፈፅሙ አካላትን ለፀጥታ ኀይሉ አጋልጦ በመስጠት ለፖሊስ ተባባሪ መሆን ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።




