በደቡብ ጎንደር ዞን በይፋግ ንዑስ ፖሊስ ጣቢያ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
ዋና ሳጅን ያለው ሞላ የይፋግ ንዑስ ፖሊስ ጣቢያ የመንገድ ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው ከጎንደር ወደ ባህር ዳር በሚጓዝ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ነው።
መኪናው 18 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ልዩ ቦታው አምባርጌ ዘይት ፋብሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቆመ FSR የጭነት መኪና ጋር ተጋጭቶ መገልበጡን ተናግረዋል።
እንደ ዋና ሳጅን ያለው ሞላ ገለጻ አሽከርካሪውን ጨምሮ የ7 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግረው 7 ከባድ እና 4 ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን የአካባቢውን ህዝብ በማስተባበር አዲስ ዘመን ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልፀዋል።
አደጋው የደረሰው ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር መሆኑን ያነሱት ዋና ሳጅን ያለው አሽከርካሪዎች ህግና ስርዓትን አክብረው በማሽከርከር በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ መከላከል ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።



