“የሚከናወኑ ሁነቶች ያለምን የትራፊክ አደጋ እንዲጠናቀቁ ሁሉም የፀጥታ ኀይል የሚጠበቅበትን ኀላፊነት ሊወጣ ይገባል” ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ

“የሚከናወኑ ሁነቶች ያለምን የትራፊክ አደጋ እንዲጠናቀቁ ሁሉም የፀጥታ ኀይል የሚጠበቅበትን ኀላፊነት ሊወጣ ይገባል” ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ

የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዋና መምሪያ የ100 ቀናት የዕቅድ ውይይት አካሂዷል።

ዋና መምሪያው በመጭዎቹ 100 ቀናት ውስጥ እንደ ክልል በሚተገበሩ የትራፊክ ቁጥጥር ተግባራት ዙሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት ነው የዕቅድ ውይይቱ የተካሄደው።

ዕቅዱን ያቀረቡት ኢንስፔክተር ሰጠኝ አለሙ የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዋና መምሪያ ሪፖርት እና ስታስቲክስ ባለሙያ እንደገለጹት እየተበራከተ የመጣውን የመንገድ ትራፊክ አደጋን ለመከላከል በትኩረት መሰራት ይገባል ብለዋል።

በክልላችን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት እና ቁጥጥር ማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የመንገድ ትራፊክ አደጋን መቀነስ እንደሚገባ በዕቅድ ውይይቱ ተመላክቷል።

በዕቅድ ውይይቱ ላይ የተገኙት ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ እንደተናገሩት በክልሉ ውስጥ የሚከወኑ ሁነቶች ያለምንም የፀጥታ ችግር እና የትራፊክ አደጋ እንዲጠናቀቁ ሁሉም የፀጥታ ኀይል የሚጠበቅበትን ኀላፊነት ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ በህዝብ ዘንድ ታዕማኒነት ያለው የትራፊክ ቁጥጥር ስራን በመስራት በህግ የበላይነት የሚያምን ማህበረሰብ ለመፍጠር በቁርጠኝነት እና በታማኝነት ኀላፊነትን መወጣት እንደሚያስፈልግ ረዳት ኮሚሽነር አበበ ተናግረዋል።

የነበሩ ጠንካራ ተግባራትን በማስቀጠል እና ክፍተቶችን በማረም ዕቅዱ የተፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ሁሉም አካል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት ይገባዋል ያሉት ረዳት ኮሚሽነር አበበ ውቤ ከትራፊክ አደጋ ስጋት የተላቀቀ ክልልን እውን ለማድረግ በትብብር መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top