የታጠቁ ኀይሎች በሰላማዊ መንገድ እጅ ሰጡ
በደቡብ ጎንደር ዞን ወደ ጫካ ገብተው የነበሩ በርካታ የታጠቁ ሃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በሰላማዊ መንገድ ለመከላከያ ሰራዊት እጅ መስጠታቸውን የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል።
በዞኑ ጸዳሉ ደሴን ጨምሮ በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጮችን እየተቀበሉ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ታጣቂዎች መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀበለው እጅ ሲሰጡ የክልል፣ የዞንና የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።
አቶ ጥላሁን ደጀኔ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ እንደተናገሩት መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ በመቀበል በሰላማዊ መንገድ እጅ መስጠታችሁ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በአካባቢው ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ሌሎች ሀይሎችም የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ ጥሪ ቀርቧል።





