በሠላምና ፀጥታ፣ ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ፓኬጆች አተገባበር እና የህግ ማስከበር አፈፃጸም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው
በደብረ ብርሃን ከተማ የሠላምና ፀጥታ፣ የኀይል ማሰባሰብ፣ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ፓኬጆች አተገባበርና የህግ ማስከበር አፈፃጸም ግምገማና የቀጣይ አቅጣጫን የሚያመላክት ውይይት ተጀመረ።
በውይይቱ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ በድሉ ውብሸት፣ የአማራ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ አማካሪ ኮሎኔል ባምላኩ አባይ፣ የደብረ ብርሃን ከተማ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ዳንኤል እሸቴን ጨምሮ የፀጥታ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን የደብረ ብርሃን ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት አበበ ለውይይት መነሻ ዋና ዋና የአፈፃጸም ሪፖርት እያቀረቡ ነው።




