“የፖሊስ የከፍታ ዘመን ይሆናል” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

“የፖሊስ የከፍታ ዘመን ይሆናል” ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

ሚያዚያ 29/1901 ዓ.ም የተመሰረተው ዘመናዊው የኢትዩጲያ ፖሊስ 116 ዓመታትን አስቆጥሯል። ዓመታትን በተሻገረው በዚህ ሂደት በበርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች የሚጠበቅበት ያህል ውጤታማ አይደለም። በዚህም የተነሳ የሀገራችን ፖሊስ የተሳካ ጠንካራ የተቋም ግንባታን አልታደለም።

የህዝብን ሰላምና ደህንነትና በገለልተኝነት የመጠበቅ ኀላፊነት የተጣለበት ይህ ተቋም በመርህ አገልግሎት ባለመስጠቱ ምክንያት የተለያዩ ትችቶችንም የሚያስተናግድ መሆኑ ሪፎርም ለማድረግ አስገድዷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ የፀጥታ ተቋማትን ሪፎርም ለማድረግም ለወራት በጥናት የተመሰረተ የአደረጃጀት ማሻሻያ ሲደረግ ሰንብቶ የማብሰሪያ መርሀ ግብሩ ዛሬ ግንቦት 2/2017 ዓ.ም ተከናውኗል።

የአማራ ክልል ፖሊሰ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ለውጥ የግድ የሆነው በተለመደው መንገድ የህብረተሰቡን የፖሊስ አገልገሎት ጥያቄ ማስተናገድ ባለመቻሉ መሆኑን ጠቅሰው ተቋሙ በህግ በግልፅ የተሰጡትን ተልዕኮ በሚወጣበት አግባብ ይደራጃል ብለዋል።

ፖሊስ አለም አቀፋዊ በራሱ የሙያ ስነምግባር የሚመራ የተከበረ ሙያ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ለህዝብ የሚቆረቆር፣የገባውን ቃል ኪዳን የሚጠብቅና የሙያ ፍቅር ያለው እንዲሆን በዶክትሪን ይመራል ብለዋል።

ፖለቲካ፣ሀይማኖት፣ሌብነትና ጎጠኝነት ለፖሊስ ቀይ መስመሮች ናቸው ያሉት ክቡር ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ መጭው ጊዜ የፖሊስነት ከፍታ እንዲሆን እንሰራለን ብለዋል።

የመርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ዘመኑን የሚመጥን በቴክኖሎጅ የተደገፈ ሁሉን አቀፍ ሪፎርም እንዲከወን አሳስበው በሁለንተናዊ ተቋማዊ ሂደት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አሳስበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top