
ለኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ አቀባበል ተደረገላቸው።
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ለተመደቡት ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በኮሚሽኑ የማኔጅመንት አባላት እና መኮንኖች የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የሰው ኃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ የተቋሙን አመራሮች እና አባላትን በመወከል አዲስ የተመደቡትን ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴን እንኳን ደህና መጡ ብለዉ በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ለህብረተሰቡ ሰላም በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በበኩላቸው ፖሊሳዊ ብቃት እና ስብዕናን የተላበሰ የተሰጠውን ተልዕኮ የሚወጣ ዘመናዊ ፖሊስ እና አደረጃጀት በመፍጠር የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በጋራ እና በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል።