በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በጓንጓና በዚገም ወረዳ አጎራባች ቀበሌዎች ግጭት ፈጥረው በዘረፉ የተሳተፍ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በጓንጓና በዚገም ወረዳ አጎራባች ቀበሌዎች ግጭት ፈጥረው በዘረፉ የተሳተፍ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በጓንጓ ወረዳ በይማሊ ቀበሌና በዚገም ወረዳ በፂውሊ ቀበሌ መካከል ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግርን ለመፍታት የህዝብ ለህዝብ ውይይት መድረክና የእርቀ ሰላም ፕሮግራም ተከናውኗል።

በእርቀ ሰላም ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እሱባለው መኮነን በጓንጓና በዚገም ወረዳ አጎራባች ቀበሌዎች

በ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጠረው ግጭት የሁለቱም ወረዳ ወንድም ህዝቦች ተለያይተው የቆዩትን በሀገር ሽማግሌዎች፣ በሀይማኖት አባቶችና በአመራሩ ቁርጠኝነት ችግሩ ተፈቶ እርቀ ሰላም መውረዱ ፍትህን ለማረጋገጥ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ተናግረዋል።

በማህበረሰቡ መካከል ግጭት ፈጥረው ከሁለቱም ወገን ሀብት የዘረፉትን ግለሰቦች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ሀብት ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱና ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን የጠቀሱት መምሪያ ኃላፊው ለቀጣይ በየደረጃው የሚገኝ የፖሊስ አባሉ የሰው ህይወት የሚያጠፉና ሀብት የሚዘርፉትን ከማህበረሰብ ጋር በመሆን በህግ ጥላ ስር ለማዋል እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የጓንጎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ቦጋለ በበኩላቸው የጓንጓና የዚገም ወረዳ አጎራባች ቀበሌዎች ለዘመናት ችግርና ደስታ ተከፋፍለው በጋራ የኖሩትን ማህበረሰብ የግል ጥቅም ፈላጊዎች በመካከላቸው ግጭት ፈጥረው ሀብት በመዝረፋቸው በማህበረሰብ ላይ ቅሬታ እንደነበር ገልፀው የተዘረፉ ንብረቶች በሀገር ሽማግሌዎችና በሀይማኖት አባቶች ጥረት እየተመለሱ ነው ብለዋል።

የዚገም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካም አለነ እንደገለፁት በፊት የነበረውን የአንድነትና አብሮነት ለመመለስ ተከታታይ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ማካሄዳቸውን ገልፀው በሀገር ሽማግሌዎች፣በሀይማኖት አባቶችና በአመራሩ ቁርጠኝነት ዘላቂ የሰላም ሂደት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ በሁለቱም ወረዳዎች 14 አባላት ያለው ኮሚቴ የተቋቋመው መሆኑንም አቶ መልካም ተናግረዋል።

ለዓመታት ተሳስረው ከኖሩበት ማህበረሰብ የተደራጁ ሌቦች በፈጠሩት ግጭት ንብረት በመዘረፋቸው ተለያይተው እንደቆዩ

የዚገምና የጓንጓ ወረዳ አጎራባች ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል አቶ ጌታነህ ብርሃኑ ፣ አቶ ውማክ ባንጃና አቶ ወርቁ ሙሀመድ ገልፀው ዘራፊዎች የፈጠሩት ችግር በሀገር ሽማግሌዎች ፣ በሀይማኖት አባቶችና በአመራሩ በለሰለሰ ጥረት ችግሩ እየተፈታ በመሆኑ ቀጣይ በአንድነትና በአብሮነት ኑራቸውን እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል ።

መረጃው፦የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top