በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የባህርዳር እና የጎንደር ቀጠና የፖሊስ አመራሮችና አባላት የጅኦ ስትራቴጂካዊ እና የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና ተጀምሯል።

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የባህርዳር እና የጎንደር ቀጠና የፖሊስ አመራሮችና አባላት የጅኦ ስትራቴጂካዊ እና የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና ተጀምሯል።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው በዕለቱ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የአማራ ክልል ፖሊስ የተጣለበትን ክልላዊ እና ሀገራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት በየጊዜው ሰፊ ተግባራትን በመከወን የክልሉን ሰላምና ልማት ለማስጠበቅ የሚተጋ ተቋም ከመሆኑም ባሻገር በየጊዜው በሚሰሩ የለውጥ ስራዎች ራሱን ያደረጀ ተቋም ነው ብለዋል።

በክልሉ የተከሰቱ ግጭቶችን በማረጋጋት እና ሀገር የማፍረስ ሴራን ለመቀልበስ የህይወት መስዋዕትነትን ጭምር በመክፈል የአማራ ክልል ፖሊስ ሰራዊት ከአጋር የጸጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት አይተኬ ሚና ተወጥቷል ሲሉ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው አብራርተዋል።

የክልላችንን ብሎም የሀገራችንን ሁኔታ የተረዳ፣ በስነልቦና የተዘጋጀና ህዝብን ለማገልገል ለመስዋዕትነት የማያመነታ የፖሊስ ኃይል መፍጠር ያስፈልጋል።

እንደ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጻ ስልጠናውም የሰራዊቱን ወትሮ ዝግጁነት የሚያጎለብትና የተከናወነው የፖሊስ ሪፎርም ስኬታማ እንዲሆንና በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ መስማማትና በበቂ መረጃ ላይ የተመሰረተ ግንዛቤ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

ወንጀልንና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በመከላከል እና ሰላምን በማስፈን ሂደት የአመራሩ ድርሻ ጉልህ በመሆኑ ይሄን ተገንዝባችሁ የበኩላችሁን ልትወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ሞራል ያለው እና በስነልቦናው የበላይ የሆነ ሰራዊት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የባህርዳር ከተማ አስተዳደር አስፈላጊውን ሀሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው አስገንዝበዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው በበኩላቸው ለሀገር ክብርና ደህንነት፣ ለዜጎች ሰላምና ለህግ የበላይነት መከበር ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የፖሊስ ተቋም ነው ብለዋል።

ስልጠናውም የሪፎርሙን ጉዞ እና የወደፊቱን ራዕይ ለማስተዋወቅ እንዲሁም የተጀመረው ሪፎርም ወደ ተግባር በመቀየር እና በሚፈለገው ፍትሀዊ የሆነ የአገልጋይነት ስነ-ልቦናን በመላበስ የፖሊስ ተቋሙን የከፍታ ጉዞ የሚያመላክት መሆኑን አስረድተዋል።

በተለያዩ የፖሊስ የአመራርነት ሙያ ላይ አለም የደረሰበትን የቴክኖሎጅና የፕሮፌሽናልሊዝም ደረጃ የተገነዘበ የፖሊስ አመራር ለመፍጠር ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል።

የህዝብ እምነት የፖሊስ ስራ ስኬታማነት ዋና መሰረት ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነሩ የህብረተሰብ ተኮር የፖሊስ አገልግሎትን በማጠናከር ፖሊስን ከህዝብ ጋር አቀናጅቶ በመስራት የወንጀል መከላከል ስራችን ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው አክለውም ዘመናዊ የፖሊሳዊ አመራርነት ጽንስ-ሀሳቦች ከትዕዛዝና ቁጥጥር ወደ ለውጥ አምጪ አመራር እና አገልጋይ አመራር ተሸጋግሯል ብለዋል።

አቶ ቻላቸው ዳኜ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎንደር ከተማ እየተሰጠ ባለው የፖሊስ አመራሮችና አባላት የሪፎርም አፈጻጸም እና የአመራር አቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ፖሊስ ተቋም የጀመረው ለውጥና የከፍታ ጉዞ የሚበረታታና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው በማለት አስገንዝበዋል።

ፖሊስ ተቋም ዝቅ ሲል የሀገር ክብር አብሮ ዝቅ ይላል፤ ፖሊስ የሀገር መልክ ነው በመሆኑም አሁን ላይ ተቋሙ እያደረገው ያለውን ለውጥና ሪፎርም ሁላችንም መደገፍ አለብን ብለዋል።

ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ ምክትል ኮሚሽነር እና የአስተዳደር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ የፖሊስ ተቋም የ116 ዓመት ታሪክ ያለው የሀገር ዋልታና ማገር የሆነ ተቋም ነው። ይህ አንጋፋ ተቋም አሁን ላይ ዘመኑን የሚመጥን ሪፎርም እያደረገ ነው ብለዋል።

እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ ሙያዊ ስነ-ምግባርን በላቀ ደረጃ በማሳደግ እና በማዳበር የዜጎችን መብት ባከበረ መልኩ የፖሊስን ተግባር መከወን ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

ሪፎርም በሰነድ ላይ የሚቀመጥ ጽሑፍ ሳይሆን ሰርተን የምንለወጥበት እና ወደ አዲስ አሰራር ገብተን ተቋሙ እንዲቀየር የምንተጋበት መሆኑን ነው ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ ምክትል ኮሚሽነር እና የአስተዳደር እና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ጎንደር ከተማ እየተሰጠ ባለው የፖሊስ ስልጠና ላይ ያብራሩት።

በስልጠናው መክፈቻ የተቋሙን የ116 ዓመት ጉዞ እና አሁን አየተጓዘበት ያለውን የከፍታ ጉዞ የሚያሳይ የዶክመንተሪ ፊልም ቀርቧል።

ስልጠናው በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለሚገኙ የፖሊስ ሰራዊቱ የሚሰጥ መሆኑ ተመላክቷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top