የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያሰለጠናቸውን የ34ኛ ዙር የመደበኛ እና አድማ መከላከል ምልምል ፖሊሶችን አስመርቋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያሰለጠናቸውን የ34ኛ ዙር የመደበኛ እና አድማ መከላከል ምልምል ፖሊሶችን አስመርቋል።

ለአንድ ሀገር ልማትና እድገት መረጋገጥ አስተማማኝ የሰላም ሁኔታ እና አስተማማኝ የጸጥታ ኃይል የመኖር አስፈላጊነት የሚያጠራጥር አይደለም።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያሰለጠናቸውን የ34ኛ ዙር የመደበኛ እና አድማ መከላከል ምልምል ፖሊሶችን አስመርቋል።

በብር ሸለቆ መሰረታዊ የውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የ34ኛ ዙር የመደበኛ እና አድማ መከላከል ምልምል ፖሊሶችን ነው ያስመረቀው።

ምክትል ኮሚሽነር አበበ ደለለ የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት ክልላችን ከገባበት የጸጥታ ችግር ለመውጣት በሚደረገው ጥረት የአንበሳውን ድርሻ የምትወጡት የሰላምና ደህንነት ማሳለጫ ተዋናዮች እናንተ ናችሁ ብለዋል።

በስልጠና ያገኛችሁትን ልምድና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል ያሉት የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ፕሬዝዳንት ፖሊሳዊ ሙያውን እና ስነ-ስርዓቱን ባከበረ መልኩ ኃላፊነትን መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል።

የዛሬ ተመራቂ ፖሊሶች ከወትሮው ልዩ የሚያደርጋችሁ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ባደረገው ሪፎርም መሰረት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ወደ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ባደገበት ማግስት መሆኑ ነው ብለዋል።

ወንጀል ፈጻሚዎች በህዝብ ላይ በደል እንዳይፈጽሙ ቆርጦ በመነሳት እና በመፋለም ሰላምን ማጽናት ይገባል ብለዋል።

የአንድነት መጓደል ተገርስሶ ወደ ሰላምና ልማት ለመሸጋገር ተስፋ የሰጠ ስልጠና መሆኑን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ የክልላችን ሰላም በራሳችን ጣምራ ክንዶች እና መስዋዕትነት ማስከበርና ማስጠበቅ ይገባል ብለዋል።

ብርጋዴር ጀነራል መኮንን መንግስቴ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዋና አዛዥ በበኩላቸው ከክልል የተሻገረ ሀገራዊ ኃላፊነት የተሰጣችሁ በመሆኑ የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ሰላም ማስጠበቅ ይኖርባችኋል ብለዋል።

ከሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ባንዳዎች ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመሆን በህዝባችን ላይ ያወጁብንን ሳንካ ነቅሎ ለመጣል ከወትሮው በተለየ መልኩ ታትሮ መስራት ይጠይቃል ሲሉም ብርጋዴር ጀነራል መኮንን መንግስቴ አክለው ገልጸዋል።

ተመራቂ ኮንስታብል ኪሩቤል አበበ በበኩሉ ቀደም ሲል ስለ ፖሊስ የነበራቸው ጥሩ አመለካከት ፖሊስ ለመሆን እንደገፋፋቸው ገልፀው ለሀገራችን ደህንነት እና ለህዝባችን ሰላም እስከ ህይወት መስዕዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል።

በማሰልጠኛ ማዕከሉ ያገኘነው ስልጠና ከወታደራዊ ስልትና አካል ብቃት፣ ስነስርዓት በተጨማሪም ለቀጣይ ህይወት የሚጠቅሙ የህይወት መርሆዎችን ያስገኘልን ነው ይህንን ስልጠናም ወደተግባር በመቀየር ህዝባችንን ማገልገል የወጣንበት ዓላማ ነው ብለዋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይም የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተመራቂዎች እና ለስልጠናው ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት የዕውቀትና እና ሽልማት መርሐ-ግብር ተካሂዷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top