እንኳን ደስ አላችሁ!!
እንግሊዝ በተደረገ የ21 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር የአማራ ክልል ፖሊስ አትሌቲክስ ቡድን አባል የሆነው ኮንስታብል ይስማዉ ድሉ 1ኛ በመውጣት አሸንፏል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሪፎርም ስራን፣ የዲጂታላይዜሽን ማብሰሪያ እና የአዲስ ሕንፃ የምረቃ መርሀ-ግብርን ባካሄደበት ዕለት ኮንስታብል ይስማዉ ድሉ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን ማሸነፉ ደስታችንን ድርብ ያደርገዋል።
በመሆኑም የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) ለመላው ፖሊስ ሰራዊት አመራር እና አባላት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።



