የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጀመረውን የሪፎርምና የዲጅታላይዜሽን ማብሰሪያና አዲስ ህንፃ ምረቃን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጀመረውን የሪፎርምና የዲጅታላይዜሽን ማብሰሪያና አዲስ ህንፃ ምረቃን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት በአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ሲያከናውን የቆየው ሁሉን ዓቀፍ የሪፎርም ስራ፣ ዲጅታላዜሽን ማብሰሪያና አዲስ ህንፃ የምናስመርቅበት ስራ በስኬት ተጠናቀው ለመመረቅ መብቃታቸው ፖሊስ ተቋሙ የጀመረውን የከፍታ ዘመን ጉዞ አጉልተው የሚያሳዩ መነፅሮች ናቸው ብለዋል።

ሁነቱን ልዩ የሚያደርገው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በተመረቀበት ማግስት እና የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን በጀመረችበት ወቅት መሆኑ ነው ብለዋል።

የተተገበረው የሪፎርም ስራ በሁሉም ዘርፎች አመርቂ ውጤትን ማስመዝገብ የሚያስችል ሲሆን በወንጀል መከላከል ዘርፉ ቴክኖሎጂን መጠቀም የሚያስችል አሰራርን ያበሰረ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የተጀመረውን የህግ ማስከበር ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል እና በአጭር ጊዜ ወደ ቀደመ ሰላሙ የሚመለስመሆኑን እገልጻለሁ።

ተቋሙ ትልቅ ስኬት የሆነው እና መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም የሚመረቀው አዲሱ ባለ ሰባት ወለል ህንፃ ማስፋፊያ ደረጃውን የጠበቀና ለወንጀል ምርመራ ስራ አጋዥ የሆኑ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ያሟላ እና የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ በጠበቀ መልኩ የምርመራ ክፍሎችን ያካተተ ነው ብለዋል።

በሪፎርሙ ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር በሁሉም ዞኖች አዲስ የህንጻ ዲዛይን ተዘጋጅቶ ግንባታ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን ያስታወቁት ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ የጀግኖች ማዕከል ግንባታንም ለማስጀመር በደብረብርሃን ከተማ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል ብለዋል።

ለመላው የክልሉ ፖሊስ ሰራዊት እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ! ያሉት የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዋና መምሪያ ኃላፊው በሁሉም ዘርፍ የተጀመረው የሪፎርም ስራ ውጤታማ እንዲሆን ትልቅ ኃላፊነት ከሁሉም የፖሊስ ሰራዊት ይጠበቃል ብለዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top