“የፖሊስን ዋጋ እና ክብር የሚመጥን የጀግኖች ማዕከል ነው የሚገነባው” ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር)

“የፖሊስን ዋጋ እና ክብር የሚመጥን የጀግኖች ማዕከል ነው የሚገነባው” ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር)

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጀግኖች ማዕከል ግንባታን በደብረ ብርሃን ከተማ አስጀምሯል።

ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዘዥ የፖሊስን ዋጋ እና ክብር የሚመጥን ማዕከል ነው የሚገነባው ብለዋል።

ኮሚሽነሩ ለማኅበረሰቡ ሲል ዋጋ የከፈሉ የፖሊስ አባላት ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ እና እንዲቋቋሙ የሚያስችል ማዕከል የሚገነባ ስለመሆኑም አንስተዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የማዕከሉ ግንባታ እንዲፋጠን አስፈላጊውን መሠረተ ልማት በማሟላት ከተማ አሥተዳደሩ ኀላፊነቱን ይወጣል ብለዋል።

ለከተማው ልማት እና ለሀገር እድገት የፖሊስ ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ይህንን ውለታቸውን በአግባቡ መክፈል ይገባልም ነው ያሉት።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የክልል፣ የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞን የስራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top