“ጽናት የሚረጋገጠው በደም እና በአጥንት በሚከፈል እውነተኛ መስዕዋትነት ነው” ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)

“ጽናት የሚረጋገጠው በደም እና በአጥንት በሚከፈል እውነተኛ መስዕዋትነት ነው” ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)

ጳጉሜን 1 የጽናት ቀን በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት በልዩ ልዩ ስነ-ስርዓት እየተከበረ ነው።

በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)፣ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ፣ መንገሻ ፈንታሁን (ዶ/ር) የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የመከላከያ፣ የፌዴራል እና የአማራ ክልል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

“ጽናት የሚረጋገጠው በደም እና በአጥንት በሚከፈል እውነተኛ መስዕዋትነት ነው” ሲሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ለፈተናዎች ባለመንበርከክ እና ጸንቶ በመቆም ለሀገር እድገት እና ለህዝብ ደኅንነት መስዕዋት ለከፈላችሁ የመከላከያ፣ የፌዴራል እና የአማራ ክልል ፖሊስ፣ ለብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት እንዲሁም ለሚሊሻ እና ሰላም አስከባሪዎች ክብር ይገባችኋል ብለዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top