“የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ቀን ከሌት መስራታችን ይቀጥላል።” ኮማንደር ሽመልስ ኃይሉ የአድማ መከላከል ፖሊስ ሻለቃ አዛዥ

“የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ቀን ከሌት መስራታችን ይቀጥላል።” ኮማንደር ሽመልስ ኃይሉ የአድማ መከላከል ፖሊስ ሻለቃ አዛዥ

የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ሰላም ለማስጠበቅ የህይወት ዋጋን እየከፈሉ ከሚገኙ የፀጥታ መዋቅር መካከል የአማራ ክልል አድማ መከላከል ፖሊስ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።

የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ እና ህግ ለማስከበር ውሎ አዳራቸውን ምሽግ ካደረጉ የአድማ መከላከል ፖሊስ መካከል በምስራቅ ጎጃም ዞን እና አካባቢው ከሚገኘው የ34ኛ ሻለቃ አድማ መከላከል ፖሊስ አመራርና አባላት ጋር ቆይታ አድርገናል።

የሻለቃው አዛዥ ኮማንደር ሽመልስ ኃይሉ እንደተናገሩት የክልሉ ሰላም ነፃ እናወጣሀለን በሚሉ አካላት መደፍረሱን ተከትሎ ህዝባችን ዘርፈ ብዙ መከራዎችን እያስተናገደ በመሆኑ በክልሉ ሰላም ተረጋግጦና ማህበረሰቡ ወደ ልማት ተመልሶ እስካላየን ድረስ ህግ የማስከበር ተግባራችን እና ተጋድሏችን ይቀጥላል ብለዋል።

ሰራዊቱ በፈተናዎች የተገነባ፣ በሁኔታዎች ያለፈ መሆኑን ያነሱት ሻለቃ አዛዡ “አላማችን የአማራን ህዝብ ደህንነት ማረጋገጥ እና የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ማድረግ ስለሆነ ቀን ከሌት መስራታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

በቀጣይም ህገወጥ ታጣቂ ኃይሉ በመንግስት የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ እስኪመጣና የተረጋገጠ ሰላም እስኪሰፍን የምናካሂደው ህግን የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት ኮማንደር ሽመልስ ኃይሉ።

ብሬን ተኳሹ ምክትል ሳጅን ታዘበው ውቤ በበኩሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተቋቁመን የምናደርገው ህግ የማስከበር ዘመቻ አላማው የህዝብን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ በመሆኑ ደስተኞች ነን ሲል ተናግሯል።

የታጠቁ ኃይሎች በበሬ ወለደ ፕሮፖጋንዳ የሚያመጡት ለውጥም ሆነ ድል የለምና የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴያቸው እንዲመለሱ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ቆይታ ያደረጉ የአድማ መከላከል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት መልዕክት አስተላልፈዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top