የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውጤታማ ስራወችንን ማከናወኑን አስታወቀ።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በምርመራ ዘርፉ ውጤታማ ስራዎች መከወናቸውን የኮሚሽኑ የምርመራ ዘርፍ አስታውቋል።
በኮሚሽኑ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ምክትል ዘርፍ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ እንደገለጹት ምርመራን በጥራት አጣርቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ በኩል ሰፊ ስራ የተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በዘጠኝ ወሩ በተከናወኑ የምርመራ ስራዎች የታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ተከሳሽ እና ምስክሮችን ተከታትሎ ባለማቅረብ የተዘጉ መዝገቦች በምርመራ ስራው ላይ ከፍተኛ እንቅፋቶች እንደፈጠሩ ያነሱት ኀላፊው የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይንሳዊ የምርመራ ስራዎችን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸቸው ያለፈውን ክፍተት በመሙላት ለቀጣይ ስራ በተነሳሽነት በመስራት የምርመራ ጥራትን አስጠብቆ ፍትህን ለማስፈን የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።




All reactions:
206206