የተለያዩ የሺሻ መጠቀሚያ እቃዎችን መያዙን ፖሊስ ገለፀ።

የተለያዩ የሺሻ መጠቀሚያ እቃዎችን መያዙን ፖሊስ ገለፀ።

በባህርዳር ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በተደረገ ፍተሻ በርካታ የሺሻ መጠቀሚያ ዕቃዎችን መያዙን በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ፍሬው ተናግረዋል።

የሽሻ መጠቀሚያ ዕቃዎቹ ከማህበረሰቡ በተገኘ ጥቆማ የተያዙ ናቸው ያሉት ኢንስፔክተር ተስፋዬ ፍሬው ይህንን ህገወጥ እና ለወንጀል አጋላጭ ተግባር የሚያጨሱና የሚያስጨሱ አካላት ላይ ጠንከር ያለ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል።

የሺሻ ማስጨሻ ቤቶች የወንጀል ድርጊትን ለመፈፀም የሚያስችል ዕቅድ የሚወጣባቸው ቦታዎች ስለሆኑ ሁሉም ማህበረሰብ ለፀጥታ ኃይሉ ጥቆማ በመስጠት ተባባሪ ሊሆን ይገባል ሲሉ ኢንስፔክተር ተስፋዬ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top