በኤሌክትሪክ ታወር ላይ ስርቆት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ ከኮምቦልቻ ቁጥር 2 እስከ ኮምቦልቻ ቁጥር 1 በተዘረጋ 132 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ በኤሌክትሪክ ታወር ላይ ስርቆት የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የቃሉ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ምክትል ኮማንደር ሙሉጌታ በለጠ እንደተናገሩት በቃሉ ወረዳ 07 ቀበሌ ልዩ ቦታው ቀዲዳ በተባለ ቦታ በኢትዮዮያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ ታወር ላይ ስርቆት በመፈጸም አገልግሎቱ እንዲቋረጥ በማድረግ ህዝቡ እንዲቸገር ያደረጉ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
ፖሊስ በጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ የጀመረ እና በፍርድ ቤትም ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ምክትል ኮማንደሩ ጨምረው ገልጸዋል።
መረጃው የቃሉ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ነው።

