
በከተማ አስተዳደሩ አሁን የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል ውይይት ተካሄዷል
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የጸጥታ ተቋማት የአድማ መከላከል አመራሮችን ጨምሮ አሁን የተገኘውን ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል ውይይት ተካሄዷል።
በውይይቱ በከተማው ይፈጸሙ የነበሩ የእገታን እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወንጀሎችን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የተገኙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ከፍትህ ተቋማት ጋር በአጭር ግዜ ውሳኔ ማሰጠት መቻሉ በአወንታዊ ተነስቷል።
ፅንፈኛው ቡድን ከተማው ላይ ጉዳት እንዳያደርስ
የፀጥታ ተቋማቱ እያከናወኑት ያለው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑም ተጠቁሟል።
የጠላትን ሀይል አከርካሪ በመስበር እና በመደምሰስ ብሬንን ጨምርሮ ሌሎች መሣሪያዎችን እና ተተኳሾችን መማረክ መቻሉ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑም በውይይቱ ተነስቷል።
አሁን ላይ የተጀመረውን የህዝብ የጥበቃ አደረጃጀጀት በማስፋት ህብረተሰቡ ከጸጥታ ሀይሉ ጎን ተሰልፎ ወንጀልን በብቃት መከላከል የሚችልበትን አሰራር አጠናክሮ በማስቀጠል ሰላምን ማጽናት የሚያስችል ውይይት መካሄዱን ከደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።