ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

በአዲስ መንፈስና እሳቤ ለአዲስ ተስፋ ራሳችንን እናዘጋጅ!! ህዝባችን ሰላማዊ ነው ሰላምን አጥብቆ ይፈልጋል፡፡ በመርህና እውነት ፤በህግና እምነት የሚመራ የፍትህ ባለቤት ነው፡፡ ይህንን ማረጋገጥ ደግሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ተቋማዊ ሚና እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በእርግጥ ነገሮች እንደ ህዝቡ እሴት አልሆን ብሎ በተደጋጋሚ በሚስተዋል የሰላም እጦት አይነተ ብዙ ችግር ደርሷል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በክልሉ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግርም የሆነው ይኸው ነው፡፡ አሁን በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ወደ ሰላምና መረጋጋት ተመልሰዋል፡፡ ይህንን ለማጽናት የክልሉ ፖሊስ አመራሮችና አባላት ከሰብአዊነት በተቀዳ ተቋማዊ መርህ ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላምና ፍትህን ለማስፈን ስብራቶችን ለመጠገን አዲስ ተስፋ ሰንቀናል፡፡ ተግዳሮቶቻችንን ቀርፈን የህዝባችን ደህንነት በጀግንነት አንድንጠብቅ የህብረተሰቡ ትብብርና አንድነት በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡ ሁሌም በሙያዊ መርህ ተመርተን በአገልጋይነት መንፈስ የጎደለውን ሞልተን የተሻለ ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት የለውጥ ስራዎችን አጠናክረን እንደምንቀጥል ስንግልፅ በአዲስ መንፈስ ለአዲስ ሀሳብ ተዘጋጅተን ነው፡፡ ወንጀልን አስቀድመን ለመከላከል ስንተጋና ይህንኑ ተግባራችንን በመስዕዋትነት ስናረጋግጥ ለህብረተሰቡ ሰላማዊ ህይወት መከበር መሆኑን በውል ተረድተን በትብብር ለአንድነት እንድንሰለፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ በጀግንነት መጠበቅ- በሰብዓዊነት ማገልገል!! ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

Scroll to Top